/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680

ይህ የጉዳት ካሳ ክርክር የተጀመረዉ በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር 1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች፣ እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑትን ሌሎች ሶስት የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.300905 በ11/10/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ አመልካች የቡና አምራችና ነጋዴ በመሆናቸዉ ቡና ከየቡ ከተማ ካለኝ መጋዘን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ስላነሰኝ የወረዳዉን ቡናና ሻይ ባለስልጣን በአፍ በማስፈቀድ 54 ኬሻ ቡና ከጅማ ከተማ 17 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ወደ ምትገኘዉ የቡ ከተማ በመጓጓዝ ላይ ሳለሁ የይለፍ ፍቃድና ቡናዉ ቡናዉ በፕሎምፕ መታሸግ በማያስፈልግበት ሁኔታ ያስፈልጋል በማለት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አባላት ሲይዙኝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በኮሚቴ ለጉዳዩ በፍጥነት መወሰን ሲገባዉ ባለማድረጉ የያዙትን ቡና ዋጋና በገንዘቡ እስከ አሁን ብሰራበት ኖሮ ትርፉን፣ መኪናዉ ቆሞ ላጣሁት የቀን ገቢና የጠበቃ አበል እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።  የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ በኦሮሚያ ቡና ጥራት ቁጥጥርና ንግድ አዋጅ ቁ.160/2006 አንቀጽ 23 ቡናን ለማጓጓዝ የይለፍ ወረቀት እንደሚያስፈልግ፤ በቡና አዋጅ ቁጥር 602/2000 ህገ ወጥ የሆነን ቡና በመያዝ ለሚመለከተው አካል የቀረበ በመሆኑ፤ በፌደራል ደንብ ቁ.159/2001 አንቀጽ 22 (2) (ለ) ህገ ወጥ ተብሎ ለተያዘ ቡና ቅሬታ ማቅረብ የሚገባው ለሚመለከተው አካል እንጂ ለፍ/ቤት አይደለም፤ በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀጽ 19 (7) ከአቅጣጫ ውጪ እያጓገዘ በመሆኑና በፕሎምፕም ያልታሸገ በመሆኑ በህገ ወጥ የሚጓጓዝን ቡና በህጋዊ መንገድ የያዙ በመሆኑ ልንከሰስ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ ክርክር አቅርበዋል።………….

Previous Article እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155
Next Article እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798
Print
13349