Thursday, May 29, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ አበባው ታደሰ እና የአ/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የአ/ብ/ክ/መ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሰ/መ/ቁ 246690 ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 214219 ይግባኝ አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም ተጠሪዎች ያቀረብነዉን መቃወሚያ ተቀብሎ አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ሳይኖረዉ የጉባኤዉን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፡፡ጉባኤዉ ፍርድ ቤቶችን እና ዳኞችን ለማስተዳደር በሕግ ሥልጣን የተሰጠዉ ሲሆን አከራካሪዉ ጉዳይ የደመወዝ ማሻሻያ እና የኃላፊነት አበል ክፍያ በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ በመሆኑ የክርክር አመራር ሂደትን ተከትሎ አከራክሮ የወሰነዉ አይደለም፡፡ በመሆኑም ዉሳኔዉ አስተዳደራዊ እንጂ በዳኝነት ነክ አግባብ ታይቶ የተወሰነ አይሆንም፡፡በመሆኑም የክልል ሰበር ችሎት ሥልጣን ሳይኖረዉ አስተዳራዊ ዉሳኔ በመመርመር የሰጠዉ ዉሳኔ በሰ/መ/ቁጥር 92546 ላይ የተሰጠዉን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፡፡ 1ኛ የአሁን ተጠሪ በጉዳዩ ሊይ የሰጠዉ ዉሳኔ በሌለበት ዉሳኔ የሰጠዉም ጉባኤዉ ሆኖ እያለ አመልከች 1ኛ ተጠሪን በተጠሪነት በመሰየም አቤቱታ ለክልል ሰበር ማቅረባቸዉ ተገቢ አይደለም በማለት፤ ችሎቱ 1ኛ ተጠሪን ከክርክሩ ዉጭ እንዲያደርግ የቀረበለትን ክርክር ምንም ምክንያት ሳይገልጽ 1ኛ ተጠሪን የክርክሩ አካል አድርጎ የሰጠዉ ዉሳኔ የ1ኛ ተጠሪን በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1 ስር የተደነገገዉን ፍትህ የማግኘት መብት የሚቃረን ነው በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…… Print 1872 Documents to download 246690(.pdf, 862.65 KB) - 217 download(s)