Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ አባይነህ አለባቸው እና አቶ ሙሉጌታ አዳነ የሰ/መ/ቁ፡-200871 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ጎንደር ዞን ከፍኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ቤትና ይዞታን ለማስለቀቅ የቀረበውን ክርክር ተጠሪ ከሳሽ አመልካች 1ኛ ተከሣሽ በዚህ ክርክር ያልተጠሩት እማሆይ ታከለች ረታ 2ኛ ተከሣሽ እነ ወ/ሮ ነገሱ አለባቸው 4 ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩ የከተማ ቤትና ይዞታን በሚመለከት የቀረበ የመፋለም ክርክር የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ ሰኔ 12ቀን2006ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው በወረታ ከተማ ቀበሌ 02 የቤት ቁጥር 042 የሆነውንና አዋሣኙ የተጠቀሰውን ቤት የተጠሪ እናትና አባት ቤት ቢሆንም ወላጁቹ ከሞቱ በኋላ ለአመልካቹ በአደራ ተሰጥቶት እየተጠቀመበት መሆኑን እንዲያስረክበው ቢጠይቀውም ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረችዋ እማሆይ ታከለች ረታ መሬት ነው በሚል ምክንያት ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመዘርዘር ቤቱን እንዲለቅለት እንዲወሰንለት ጠይቋል፡፡………. Print 11269 Documents to download 200871(.pdf, 818.17 KB) - 920 download(s)