Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ አብዲ አህመድ ጃማ እና እአ ምባሳደር ፒተር ገብርኤል የሰ/መ/ቁጥር 214179 የጉዳዩን አመጣጥ ስንመለከተው ተጠሪዎችና የስር ከሳሾች በአመልካች ላይ በፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በጅጅጋ ከተማ ቀበሌ 05 የሚገኘውን 13838 ካሜ ይዞታ አላግባብ የያዘባቸው መሆኑን ገልፀው ይዞታውንና ቤቱን ለቆ እንዲያስረክባቸው ላቀረቡት ክስ አመልካች ባቀረቡት መልስ የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን መቃወሚያ ተቀብሎ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት በብይን የዘጋውና ይህ ብይን በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የፀና ቢሆንም ይህንን ብይን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.162536 መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ፍርድ በመሻር የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳውን መሬት በተመለከተ በአሁን አመልካች እጅ ያለው ምን ያህል ነው? መሬቱ በአሁን አመልካች እጅ ሊገባ የቻለው በምን ሁኔታ ነው? የአሁን አመልካች የገዙት ቤት ነው? ወይስ ባዶ መሬት ነው? ሽያጩ በባዶ ቦታ ከሆነ በይርጋ ክርክር ላይ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የሚለውንና መሬቱ ወደ አሁን አመልካች ያስተላለፉት ግለሰቦችም ወደ ክርክሩ በማስገባት መሬቱን እንዴት ሊያገኙ እንደቻሉ እንደዚሁም ይዞታው የሚገኝበት የጅጅጋ ከተማ ቀበሌ 05 አስተዳደር በጉዳዪ ላይ አስተያየት እንዲሰራ በማድረግና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችንም ጭምር በማጣራት እንዲወስን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.341(1) መሰረት መዝገቡን ወደ ስር ፍርድ ቤት መልሶታል፡፡መልካም ንባብ……. Print 13838 Documents to download 214179(.pdf, 833.98 KB) - 1062 download(s)