Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation አቶ አንዱዓለም ፈረደ እና እነ አለም ረዳ ወልዱ የሰ/መ/ቁ፡-208809 ጉዳዩ የመፋለም ክርክርን የሚመለከት ሆኖ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ክርክር ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ሁለተኛ ተከሣሽ አቶ ፈንታው ሰይድ አንደኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች ታሕሳስ 4ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው ዜግነታቸው ኤርትራዊያን የሆኑ ባልና ሚስት መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ በአንደኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበ ኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 05 መለያ ቁጥሩ 117 የሆነውንና በ218.5 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራውንና ግምቱ 100 ሽኅ ብር የሚያወጣውን ቤት በ1990 ዓ/ም ሁለተኛ ተጠሪ በሰራ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ሲዛወሩ ቤታቸውን እንዲያስተዳድርላቸው 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ውክልና ሰጥተው ከቆዩ በኋላ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በተደረሰው ስምምነት ተጠሪዎች ከኤርትራ ሲመለሱ የቤታቸውን ስመ-ንብረት ወደ አንደኛ ተከሣሽ (አቶ ፈንታው ሰይድ) መዞሩን አመልካች የገለፁላቸው መሆኑን በመዘርዘር ከ1991ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 2010 ዓ/ም በየወሩ 400 ብር በሚታሰብ ኪራይ በድምሩ 96 ሽህ ብር እንዲከፍላቸው፣ ቤቱንም እንዲያስክቧቸው ጠይቀዋል፡፡……………. Previous Article የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስ/ፅ/ቤት እና አቶ ሰለሞን ወዳጆ የሰ/መ/ቁ 208603 Next Article እነ አበበ ጨዶ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስ/ፅ/ቤት የሰበር መ.ቁ 212620 Print 16125 Documents to download 208809(.pdf, 538.17 KB) - 1467 download(s)