/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

አቶ አዲሱ ዓለሙ እና ወ/ሮ መስከረም ንጉሴ የሰ/መ/ቁ፡- 202486

የሰበር መዝገቡ የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ የአመልካች ሚኒባስ መኪና በሆነ ተሳፍረን በምንጓዝበት ጊዜ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በቀኝ እግሬ የታፋ አጥንት እና በግራ እግሬ ከጉልበት በታች አጥንት ስብራት በመድረሱ 28% ቋሚ አካል ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ የጉዳት ካሣ ብር 406,230.00፣ የሕክምና ወጪ ብር 90,770.00፣ የአልሚ ምግብ ወጪ ብር 2,000.00 እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 በድምሩ ብር 500,00.00 አመልካች እንዲከፍሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች የሠጡት መልስ በንግድ ሕጉ መሠረት በውል ስትጓዝ ነው ጉዳቱ የደረሰው፣ የቀረበው የጉዳት መጠን የተጋነነ የሚል ሲሆን ለመኪናው የመድን ሽፋን የሠጠው መድን ድርጅት ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ጠይቀዋል፡፡……………

Previous Article ማክሼቭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-201990
Next Article ወ/ሮ ረሂማ አብዱላሂ እና እነ ከዲር ዮሱፍ በከር የሰ/መ/ቁ፡- 202581
Print
14036

Documents to download

  • 202486(.pdf, 747.94 KB) - 1097 download(s)