/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኡስማን ሰዒድ እና በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትየሰበር መዝገብ ቁጥር 252645

ጉዳዩ የጉምሩክ ሠራተኛ የሥራ ክርክርን በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ የትኛው ነው የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበርአቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ሲሆኑተጠሪተከሳሸ ነበር፡፡አመልካች በተጠሪ መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን የተጠሪ አዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሕዳር 09 ቀን 2014 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ አመልካች ከመስከረም 08 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ከሥራ ቦታቸው ያልተገኙ በመሆኑ በፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 86(4) መሠረት ከሥራ አሰናብቷል፡፡ አመልካች ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ/ም ለተጠሪ ዋና መሥሪያ ቤት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ጥር 25 ቀን 2014 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ አመልካች በደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 42(1) መሠረት ከሥራ ቦታቸው ከቀሩ በሦስት ወር ውስጥ ለመመለስ ያላመለከቱ በመሆኑ ወደሥራቸው ሊመለሱ አይገባም በማለት አስተዳደራዊ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡መልካም ንባብ ….

Print
325

Documents to download

  • 252645(.pdf, 849.3 KB) - 55 download(s)