Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ ከሊል ሙዘይን እና እነ አቶ መንግስቱ ማሞ የሰ/መ/ቁ 205571 ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በቀን 01/08/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የኢሉ አባቦር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 35802 በቀን 03/03/2013 ዓ.ም፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መ/ቁ 224327 በቀን 12/04/2013 ዓ.ም እንዲሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀን 334676 በቀን 04/05/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ እና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የአሌ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ተጠሪ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ አመልካቾች ነበሩ፡፡ ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በወረዳ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች በቀን 30/10/2011 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ወ/ሮ ዘምዘም ቶላ በህይወት በነበረችበት ወቅት በ09/05/2011 ዓ.ም በተጻፈ ኑዛዜ ጎሬ ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኝ የቤ.ቁ 201 የካርታ ቁጥር Go/h/-253/2002 የሆነ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያላትን 3 ክፍል እና አጠገቡ ተሰርቶ የሚገኝ 4 ክፍል ያለው ንግድ ቤት፤ የካርታ ቁጥር Go/h/-264//2002 የሆነ 18 ክፍል ሰርቪስ ቤት አጠገብ ተሰርቶ ያለ ትልቅ ቤት፤ በኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ጎሬ ቅርንጫፍ የሚገኝ ብር 231,173.98 ለእኛ ለእህቶቿ ልጆች እና ለባለቤቷ ወንድም በኑዛዜ እኩል እንድንካፈል አስተላልፋ ሰጥታናለች፡፡ ሟች አክስታችን ኑዛዜ ካደረገች በኋላ በቀን 21/05/2011 ዓ.ም አርፋለች፡፡ ስለዚህ የተሰጠው ኑዛዜ እንዲረጋገጥና ባንክ የሚገኘው ገንዘብ ወደ ስማችን እንዲዛወር፤ እንዲሁም ቤቶቹም ወደ ስማችን እንዲዛወሩ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ………. Print 11379 Documents to download 205571(.pdf, 1.01 MB) - 861 download(s)