Wednesday, February 23, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ከተማ ኑኔ እና ወ/ሮ መረጠች ለማ የሰበር መ/ቁጥር 191095 በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ በሊዝ ውል የተገኘ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/14021 ላይ ታህሳስ 17/2012 ዓም በዋለው ችሎት የስር ፍቤቶችን ውሳኔ የሻረበትን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ የክርክሩ ስረ ነገር አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡ አቶ ባላይ ላጲሶ የተባሉት የአሁን ተጠሪ የቀድሞ ባለቤት ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን ጋብቻ በፍቺ መፍረሱ ተከትሎ ቦታ እና አዋሳኙ በክስ አቤቱታው ውስጥ የተዘረዘረውን እና ጋብቻቸው ፀንቶ በነበረበት ወቅት በሊዝ ውል ያገኙትን 4000 ካሬ ሜትር ይዞታ ለመካፈል በሆሳና ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ የአሁን ተጠሪም ቀርበው ንብረቱ የጋራ በመሆኑ ቢካፈሉ አልቃወምም የሚል መልስ በመስጠታቸው የተጠቀሰው ይዞታ የጋራ ንብረት መሆኑ ተጠቅሶ እንዲካፈሉ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን አመልካች ባልና ሚስቱ እንዲካፈሉ ተብሎ ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ ተጠሪና ባለቤታቸው በጋብቻ አብረው በነበሩበት ወቅት ተጠሪ ለባለቤታቸው በሰጡት ውክልና መሰረት መጋቢት 29/2008 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ያስተላለፉላቸው መሆኑን፤ በውሉ መሰረት ጉዳዩ በሚመለከተው አስተዳደር ክፍል ቀርቦ ተገቢውን ክፍያ ፈፅመው በስም ዝውውር ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን በመግለፅ ንብረቱን ባልና ሚስቱ በሽያጭ ያስተላለፋት በመሆኑ እንዲካፈሉ የተሰጠው ውሳኔ ሊሻር ይገባል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡……………. Previous Article እነ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የኢፌዲሪ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የሰ.መ.ቁ 190228 Next Article አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346 Print 12486 Documents to download 191095(.pdf, 858.27 KB) - 1132 download(s)