/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ…………….

Previous Article አቶ ወንድማገኝ ታደሰ አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 198669
Next Article አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891
Print
13132

Documents to download

  • 198805(.pdf, 727.78 KB) - 866 download(s)