Wednesday, February 23, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ዮሀንስ ክፍሉ እና አቶ ሀሰን መሀመድ የሰ/መ/ቁጥር 197942 ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ተጠሪ ለአመልካች ለቅቆ ሊያስረክብ የሚገባው በተጠየቀው ዳኝነት አግባብ በምስራቅ አቅጣጫ 1 ሜትር × 14 ሜትር ሊሆን ይገባል በማለት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን ተጠሪ በጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ነበሩ፡፡ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን በጅማ ከተማ ቦሳ ኪቶ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ 140 ካሜ መንግስት በሰጠኝ ቦታ ሰርቪስ ቤት ሰርቼበትና የይዞታ ማረጋገጫ አውጥቼበት የምጠቀምበትን በምስራቅ አቅጣጫ በኩል ወደ ይዞታዬ ርዝመቱ 1 ሜትር ቁመቱ 14 ሜትር በመግባት ግንባታ አከናውኖበት የያዘ ስለሆነ ግንባታውን አንስቶ ይዞታዬን እንዲለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡…………. Previous Article የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ እና መልካሙ ዳታ ደሴ የሰ.መ.ቁ 197432 Next Article አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ እና አቶ ወርቁ ዋበሎ የሰ/መ/ቁጥር 198071 Print 15298 Documents to download 197432(.pdf, 1.02 MB) - 1266 download(s)