Thursday, December 30, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation አቶ ደሣለኝ ሲሳይ እና ወ/ሮ ድማም ተክሉ የሰ/መ/ቁ፡-196963 የሰበር አቤቱታ የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል ነው፡፡ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ እና 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከባለቤቴ አቶ አዘነ በየነ ጋር የባንክና የዕቁብ ዕዳ ስለነበረብን በቡራዩ ከተማ ዉስጥ የነበረንን ቤት በቀን 24/08/1999 ዓ/ም በተደረገ ዉል ሽጠን በሱሉልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር ሱል/243/2005 ሆኖ የሚታወቀዉን ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ልጃችን ስለሆነ በስሙ ከአቶ ዳዊት አለሙ ላይ ገዝተናል፡፡ ይሁን እንጂ ባለቤቴ በሞት ሲለይ አመልካች ቤቱን ስለያዘብኝ ቤቱንና ሰነዱን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………….. Previous Article ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ ማኅበር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰ/መ/ቁ 196340 Next Article እነ ወ/ሮ መሠለች ደስታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የሰ/መ/ቁ.193168 Print 12883 Documents to download 196963(.pdf, 749.65 KB) - 1028 download(s)