/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

አቶ ደረጀ ቢያዝን እና ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የሰ/መ/ቁ. 216938

ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ አመልካች ከስራ የተሰናበቱት በህገ ወጥ መንገድ ስለሆነ የስድስት ወር ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራቸው ይመለሱ በማለት ወስኗል፡፡ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ያስቀርባል ካለ በኋላ ግራ ቀኙን አከራክሮ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ብይን እና ውሳኔ አፅንቶታል፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሲያፀና አመልካች እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ ውዝፍ ደሞዝ እንዲከፈላቸው አለመወሰኑን በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡ መልካም ንባብ……..

Print
10420

Documents to download

  • 216938(.pdf, 816.77 KB) - 789 download(s)