Thursday, April 1, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በመ.ቁ ከደ-2056 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 239677 በ18/3/12ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ20/4/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነውን የሰሌዳ ቁጥር 3-A37350አ.አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ የጉምሩክ ስነስርአት ያልተፈጸመባቸው ህገወጥ የኮንትሮባንድ እቃዎች ጭኖ ሲንቀሳቀስ በ28/7/10ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት አመልካች ተሸከርካሪውን እያሽከረከሩ የነበረ መሆኑ ስለተረጋገጠ በማለት በመመሪያ ቁጥር 112/08 አንቀጽ 19/20 መሰረት ተሸከርካሪው የተወረሰ ስለመሆኑ ከተጠሪ የደረሳቸውን የውርስ ውሳኔ በመቃወም ለተጠሪ አቤቱታ አጣሪ ጽ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ጽ/ቤቱም አቤቱታውን መርምሮ የውርስ ውሳኔውን በማጽናቱ አመልካች ለኢፌዲሪ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ባቀረቡት ይግባኝ አመልካች በወቅቱ አሽከርካሪው በህጋዊ መንገድ የቀጠርኩት አቶ ደምረው የሚባል ሰው መሆኑ፤ አመልካች የማሽከርከር ብቃት የሌለኝ እና የመኖሪያ አድራሻዬ መኪናው ከተያዘበት አካባቢ ስለሆነ መያዙ ተነግሮኝ ለማጣራት በቦታው እንደተገኘሁ እንዲሁም ፖሊስ ይዞኝ ቃሌን እንድሰጥ ያደረጉኝ ተደብድቤ ሲሆን በወቅቱ ቃላቸውን ሰጥተዋል የተባሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት በወንጀል ክስ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው በፍርድ ቤት ቀርበው በወቅቱ አመልካች አሽከርካሪ እንዳልነበር የመሰከሩ በመሆኑ አመልካችም መንዳት የማልችል በመሆኑ በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈው የውርስ ውሳኔ አላግባብ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበው መልስ አመልካች በምርመራ ወቅት 4ኛ መንጃ ፈቃድ ያለው መሆኑ እና ምስክር የነበሩት የፌደራል ፖሊሶች ሲያሽከረክር የነበረው አመልካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የፌደራል ፖሊሶች በፍርድ ቤት ቀርበው አመልካች ሳይሆን ሌላ ሰው ነው የሚል የምስክርነት ቃል ያልሰጡ ከመሆኑም በላይ ቃል የሰጠሁት ተገድጄ ነው ቢልም በምርመራ ወቅት መብቱ እና ግዴታው ተነግሮት ቃሉን በገዛ ፈቃዱ የሰጠ በመሆኑ በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈው የውርስ ውሳኔ በጉምሩክ አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ነው በማለት ተከራክሯል፡፡................ Previous Article እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ/መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677 Next Article ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ እና አቶ ዓሊ መሃመድ ፣ወ-ሮ ዘምዘም፣ ወ-ሮ ፎዚያ መሃመድ የሰ-መ-ቁ. 187065 Print 16743 Documents to download አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878(.pdf, 503.12 KB) - 1020 download(s)