Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ ገብረመድህን ግዛቸው እና እነ ወ/ሮ መሰረት መኮንን ሰ/መ/ቁ. 105332 የክርክር መነሻ አመልካች ኪንግ ማክሬል ካሬና ሬስቶራንት በሚል መጠሪያ በሚታወቀው የንግድ ድርጅት ውስጥ እንዲሰራ ሁለተኛ ተከሳሽ /ሁለተኛ ተጠሪ/ ያቀረበውና ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ሁለተኛ ተከሳሽ ከስራ ያባረረው መሆኑን ገልፆ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ መሰረት መብቱ እንዲከበርለት ሀምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ ክስ አቅርቧል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የለኝም፡፡ የኪንግማክሬል ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት አይደለሁም የከሳሽም አሰሪ አይደለሁም የሚል የክስ መቃወሚያ በማቅረቡ ከሳሽ /አመልካች/ የካቲት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ክሱን በማሻሻል በሁለቱ ተጠሪዎች ላይ ክሱን በማቅረብ ፍርድ ቤቱ ከሁለቱ ሰዎች ማንኛቸው ለስራ ውሉ ከህግ አግባብ ውጭ መቋረጥ ኃላፊ እንደሆኑ ለይቶ እንዲወሰንለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ መልካም ንባብ……. Print 13434 Documents to download 105332(.pdf, 823.73 KB) - 908 download(s)