/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ገብረፃድቅ ገብረኪዳን እና ፋና ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬት አክስዬን ማህበር የሰ/መ/ቁ 247466

አመልካች ያቀረቡትም ቀደም ሲል በተሰጠዉ ፍርድ ላይ ተፈፀመ ስህተት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 208 መሰረት ይታረምልኝ ሲሉ የጠየቁትን ላይ ተጠሪ አስተያየት እንዲሰጥበት ተደርጎ ጉዳዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ ተመርምሯል፡፡

አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ በግራ ቀኛችን መካከል ያለዉ ኪራይ ዉል ፀንቶ የሚቆየዉ ለአንድ አመት ከስድስት ወር ሲሆን መጋዘኑን ለማስተካከል የሁለት ወራት ተቀናሽ ተደርጎ የአራት ወራት ይከፈል ተብሎ የተወሰነ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በግራ ቀኛችን ያለዉ የኪራይ ዉል የአንድ አመት ከስድስት ወራት ስለመሆኑ ገልፆ እያለ ዉሉ የተደረገዉ ለአንድ አመት ብሎ መወሰኑ ስህተት ስለሆነ ያልተከፈለኝ ቀሪ የአንድ አመት ኪራይ ብር 3,450,000.00 (ሶስት ሚሊዬን አራት መቶ አምሳ ሺህ ብር) ተጠሪ እንዲከፍለኝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 208 መሰረት ታርሞ ይወሰንልኝ ሲሉ ጠይቋል ፡፡ተጠሪ በበኩሉ አስተያየት እንዲሰጡበት የተደረገ ሲሆን ያቀረቡት አስተያየትም አጠር ባለመልኩ ሲታይ፡-አመልካች በተጠሪ ላይ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፈል በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 208 ያቀረቡት ጥያቄ የህጉን መንፈስ ያለተከተለ ሲሆን አመልካች እያነሱ ያለዉ  ጥያቄ በፍርድ ቤት አፃፃፍ ሰህተት ሳይሆን በእራሱ የአመልካች የአፃፃፍና የማስረዳት ዉስንነት እንደሆነ የሚታይ እንጂ  በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 208 መሰረት  በቃል ወይም በቁጥር አጻጻፍ ስህተት ላይ ባልታሰበና ባለማስተዋል  በፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ የተፈፀመ ስህተት ወይም ጉድለት  በሌለበት ሁኔታ በፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ  እንደተፈፀመ ስህተት አድርገዉ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 208 መሰረት  እንዲታረም የጠየቁት ጥያቄ ተገቢነት  የለዉም የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡መልካም ንባብ ….

Print
5103

Documents to download

  • 247466(.pdf, 803.72 KB) - 560 download(s)