Wednesday, May 3, 2023 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ እና እነ ወ/ሮ ቀኑብሽ ባህታ የሰ/መ/ቁጥር-227404 ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን፣ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር በ1987 ዓ.ም ሲጋቡ አስቀድሞ ከነበረዉ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤ/ቁጥር 969 ላይ ተጨማሪ ሰባት ክፍል ሰርቪስ ቤት፣ ሁለት ማዕድ ቤትና አንድ ክፍል መጸዳጃ ግንባታ ፈጽመዉ አጥርና አርማታ ለማሰራት ብዙ ወጪ ማዉጣታቸዉን፤ ይሁንና አመልካች እና የ2ኛ ተጠሪ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ዉሳኔ ዉጪ ይህን ጨምሮ ሊከፋፈሉ አይገባም ተብሎ የንብረት መብታቸዉ ይከበርላቸዉ ዘንድ የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ… Print 308 Documents to download 227404(.pdf, 287.03 KB) - 142 download(s)