Thursday, October 7, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በመቐለ ከተማ በ02 ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.115041 በ12/09/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የአሁን ተጠሪ በቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ ትዳር ሲንመሰርት በባንክ ወደ አመልካች የሂሳብ ቁጥር ገቢ ያደረኩኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ፣ ለጥሎሽ ከሚገዛ ወርቅ ቀንሶ የወሰደዉ ብር 8190 እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝራለች። የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ለመጠየቅ መብት የለትም፣ ትዳር ሲንፈጽም ባደረግነዉ ዉል እኔም ገንዘብ በመግጠም በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ ዉስጥ የአልኮል ማከፋፈያ ከፍተን ኪራይ ብር 6000 ስንከፍል ቆይተን ስምምነት ስናጣ አሁን ለዋርድያ ብር 500 እየከፈልን እየተጠበቀ ስለሆነ ለትዳር መግጠሚያ ያቀረበችዉን ገንዘብ መጠየቋ ተገቢ አይደለም፣ በትዳር ዉስጥ ትርፍም ኪሳራም የጋራ ነዉ፣ ይህ ንብረት ተቆጥሮ በገንዘብም ሆነ በዓይነት እንዲንካፈል በማለት ተከራክሯል፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ጠቅሷል።………… Previous Article አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547 Next Article እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 Print 14892 Documents to download አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326(.pdf, 496.24 KB) - 898 download(s)