Tuesday, July 19, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ ፀጋነው መንበሩ እና አራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዬች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 208632 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ ተጠሪ የመጀመሪያ መቃወሚያዎችን አቅርቦ ተከራክሯል፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ከሳሽ ያቀረቡትን የዳኝነት ጥያቄ ለማየት ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው? ወይስ የለውም? ከሳሽ ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው? ወይስ አይደለም? የሚሉ ጭብጦችን ይዞ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ውሳኔ በዚህ መዝገብ የተጠየቀው የዳኝነት ጥያቄ አላግባብ የተወሰነ ግብርን ተንተርሶ የደረሰ ኪሳራ በሚል ኪሳራውን ለማስከፈል የቀረበ ሲሆን ግብሩ አላግባብ ተወስኗል ወይስ አልተወሰነም የሚለውን ለማየት ፍ/ቤቱ ስልጣን የሌለው በመሆኑ ይህን ተከትሎ የደረሰ ኪሳራ ለመወሰን ቀድሞ ጥፋት ባልተረጋገጠበት ሊወሰን ስለማይችል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፡፡ በሌላም በኩል ከሳሽ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 165438 ተከሳሽ አላግባብ ግብር የወሰነብኝ በመሆኑ ኪሳራ ይከፈለኝ በሚል ክስ አቅርበው ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ብሎ መዝገቡን የዘጋው በመሆኑና ውሳኔውን በይግባኝ ሳያሽሩ የገንዘብ መጠን ከፍ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይዘው መቅረባቸው አግባብ አይደለም፡፡ የተጠየቀው ዳኝነት አንድ አይነት ሲሆን ፍ/ቤቱ ወደ ፍሬ ነገር ገብቶ ያላከራከረ ቢሆንም በተሰጠው ብይን ይግባኝ ከማለት በቀር የገንዘብ መጠን ጨምሮ ክስ ማቅረብ አግባብ ባለመሆኑ የከሳሽ ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡መልካም ንባብ….. Print 11722 Documents to download 208632(.pdf, 1.01 MB) - 988 download(s)