Monday, March 8, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013 አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 ጉዳዩ የጠበቃ ዲስፕሊን ክስ ጋር በተያያዘ የተሰጠ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ በአመልካች ላይ በቀረበዉ የዲስፕሊን ክስ አቶ እሸቱ ገበየሁ እና በባለቤታቸዉ ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጋብቻ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ/ቁጥር 70064 ላይ ያደረጉትን ክርክር በፍቺ ፈርሶ የንብረት ክፍፍል ዉሳኔ በቀን 19/02/2008ዓ/ም ከተወሰነ በኋላ አመልካች የአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት ከነበሩት ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ጋር በመመሳጠር የአመልካች ባለቤት ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝ በእላዩ ላይ ቀን 11/06/2001 ዓ/ም ተብሎ ተጽፎበት በተፈረመ ዉል ለወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ብር 600,000.00 እንዳበደሩ በማስመሰል የሐሰት የብድር ዉል በመፈራረም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 177766 ላይ ባለቤታቸዉን ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝን ወክለዉ በአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት በወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ላይ ሀሰተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ክስ በመመስርት አስወስነዋል፤በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበዉ ተከራክረዋል በሚል በአቶ እሸቱ ገበየሁ የዲስፕሊን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡….. Previous Article እነ ማስተዋል ታዘበው እና ወ-ሮ አቻም ሙጬ የሰ-መ-ቁ 180761 Next Article አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331 Print 13655 Documents to download አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 (.pdf, 566.18 KB) - 1105 download(s)