/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ኢብራሒም አይዶግዱ የሰ/መ/ቁ፡-200687

 ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ከመዝገብ እንደሚታዉ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ የምግብ ባለሙያ ሁኜ በቀን 28/04/2000 ዓ.ም በወር 2500 ዶላር ደመወዝ ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ በቀን 22/08/2011 ዓ.ም ያለጥፋት ከህግ ውጪ ውልህን ጨርሰሀል በማለት ከስራዬ አሰናብቶኛል፣ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ተብሎ የአገልግሎት ክፍያ፣የካሳ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ ክፍያ የዘገየበት እና ለአውሮፕላን ቲኬት በአጠቃላይ 41,264.33 ዶላር ወይም በኢትዮጵያ ብር 1,190,477.44 ከ10% የጠበቃ አበል ጋር እንዲከፈልኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የስራ ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ ውሉ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ሊቋረጥ እንደሚችል ተስማምተናል፣ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው የስራ መደብ ላይ የኢትዮጵያ ዜጋ በብቃት ሊሰሩ የሚችሉት ነው፡፡ለአንድ የውጪ ዜጋ ደግሞ ፈቃድ የሚሰጠው የሀገር ውስጥ ሰራተኞች ግንዛቤ እና ልምድ እስከሚያገኙ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የሀገር ውስጥ ዜጎች መስራት እየቻሉ የውጭ ዜጋ መስራት የለበትም፡፡ውላችን ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ሲሆን የውጭ ዜጋ ሆኖ ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ መስራቱ ከህግ ውጪ በመሆኑ ውሉ የተቋረጠው በህግ አግባብ በመሆኑ የተጠየቀው ክፍያ ሊከፈለው አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………..

Previous Article የወ/ሮ ሐቢባ ሸምሱ ስሩር እና አቶ ቴዎድሮስ ገብሩ ብዛ ሰ.መ.ቁ.200482
Next Article ሕዳሴ ቴሌኮም አ/ማ እና እነ አቶ ገዛኸኝ ለማ የሰ/መ/ቁ፡200929
Print
11954

Documents to download

  • 200687(.pdf, 767.79 KB) - 834 download(s)