Friday, June 3, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ እነ አቶ ጋሻው ጋኔቦ የሰበር መ/ቁ/213072 ለሰበር አቤቱታ የቀረበዉ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል ነዉ፡፡ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ሶዶ ዞን ሶዶ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በተለያየ ጊዜ በመቀጠር 1ኛ ተጠሪ በነርሲንግ ስራ መደብ እና በተለያዩ የስራ ዘርፎች በወላይታ ሶዶ፣በቦረና እና በምእራብ ሀረርጌ በተለያዩ ጊዜያት የሰራ መሆኑን በመጨረሻም ከወላይታ ሶዶ ዉጭ ያሉት የድርጅቱ መስክ ቢሮዎች በስራ ላይ እያሉ የስራ ዉሉ በህገ ወጥ መንገድ በማቋረጡ ዉዝፍ ደመወዝ ከፍሎ ወደ ስራ እንዲመልሰዉ ወይም ካሳ እና ተያያዥ ክፍያዎችን እንዲከፍል እንዲወሰን ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…… Print 7622 Documents to download 213072(.pdf, 869.25 KB) - 680 download(s)