/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

ኢንፎኔት ኮሌጅ ለ የአቶ መንገሻ ታደሰ ወራሽ ወ/ሪት ፍቅርተ መንገሻ የሠ/መ/ቁጥር 198152

ጉዳዩ ለተጠሪ ይመለስ በተባለ ቤት ላይ አመልካች ከወረዳ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ጋር ያደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል እንዲፈርስ በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብሎ በቀረበ አቤቱታ መነሻ የተደረገ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡

ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ በአዉራሻቸዉ ስም ተመዝግቦ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ክልል ዉስጥ የቤት ቁጥር 1487 የሆነ ይዞታ ላይ የሚገኘዉን ቤት በቀን 26/04/1999ዓ/ም በተደረገ ዉል ለአሁን አመልካች ለ10 ዓመት አከራይተዉ የነበረዉን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 ያልተወረሰ ሆኖ እያለ የሥር 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን በመንግስት እንደተወረሰ ቤት በማስመሰል የኪራይ ዉሉን በማቋረጥ በቀጥታ ራሱ ከአሁን አመልካች ጋር ከጥር 2009ዓ/ም ጀምሮ የኪራይ ዉል በመዋዋል አከራይቶታል፡፡

Previous Article ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ እና አቶ ዓሊ መሃመድ ፣ወ-ሮ ዘምዘም፣ ወ-ሮ ፎዚያ መሃመድ የሰ-መ-ቁ. 187065
Next Article ዘሀራ ሰዒድ እና የደቡብ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መዝገቡ ሰ-መ-ቁ 193294
Print
14195