/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

እማሆይ አዛል አይናለም እና አቶ ምህረት በላይ የሰ/መ/ቁ.200144

ጉዳዩ የስጦታ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የአመልካች ክስ ይዘት ባጭሩ ለተጠሪ ያደረግሁለት የሥጦታ ውል በመንፈስ ልልነት እና በዕድሜ የገፋሁ አቅመ ደካማ በመሆኔ ምክንያት ከፈቃዴ ውጭ ህጉን ሳይከተል ያደረግሁት በመሆኑ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የስጦታ ውሉን ያፀደቀ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች በፈቃዷ ስጦታውን ያደረገችለት መሆኑን እና ክሱ የቀረበው የአመልካች ልጆች ከቅን ልቦና ውጭ በሆነ ሁኔታ መሬቱን ለመውሰድ በማሰብ ነዉ፤የስጦታ ውሉ የሚፈርስበት የህግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………….

Previous Article እነ ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ እና አቶ ብርሃኑ ሸንቆ የሰ/መ/ቁ. 199518
Next Article ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰ/መ/ቁ. 200178
Print
12928

Documents to download

  • 200144(.pdf, 526.94 KB) - 1271 download(s)