Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519 አመልካች በቀን 26/11/2015ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ - አመልካች ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ነበርኩኝ እንጂ ድርጊቱን አልፈጸምኩም፤ የተጠሪ ምስክሮች ድርጊቱን ስለመፈጸሜ አላስረዱብኝም፤ ባቀረብኩት ምስክር ወንጀሉን ያልፈጸምኩ መሆኑን አስረድቻለሁ፤የተጠሪ ምስክሮች እርሱን ይመስላል ከማለት ውጪ ድርጊቱን ስለመፈጸሜ አላስረዱም፡፡የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የወሰነዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2 ስር በተደነገገዉ መሠረት የግድያ ወንጀል መፈጸሜ ሳይረጋገጥ በመሆኑ ዉሳኔዉ ከዚህ ድንጋጌ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በሰ/መ/ቁጥር 22069 ስር የተሰጠዉን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ፡፡ስለሆነም ተጠሪ ያቀረባቸው ምስክሮች አመልካች ድርጊቱን ስለመፈጸሜ ከጥርጣሬ በላይ ያላስረዱ ስለሆነ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ እንዲጸናል፡፡የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉ የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚያጸና ከሆነም አንቀጹ ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 እንዲቀየርልኝ እና የ3ኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ስለሆንኩ ቅጣቱ በወ/ህ/አንቀጽ 192 መሰረት እንዲገደብልኝ በማለት አመልክቷል፡፡መልካም ንባብ…. Print 3660 Documents to download 251519(.pdf, 865.01 KB) - 437 download(s)