/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

እነ መ/ር ገመቹ ቹዋታ እና የየጋምቤላ ብ/ክ/መ/ ጠ/ዓ/ህግ ሰ/መ/ቁጥር 214184

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በቀን ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም በጻፈው የወንጀል ክስ በአሁን አመልካቾች እና በሌሎች 6ኛ፤7ኛ እና 8ኛ የስር ተከሳሽች ላይ በጋምቤላ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የመጀመሪያ ክስ  በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣37/1/ሀ እና 539/1/ን በመተላለፍ አመልካቾች በክሱ በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት 1ኛና 2ኛ አመልካቾች ከስር ተከሳሾችና ከሌሎች አመልካቾች ጋር በመገናኘት 2ኛ አመልካች ለግል ተበዳይ ተማሪ ቤር አጆክ ስልክ በመደወል ቴድባሌ ወደሚባል ሰፈር በመውሰድ አንገቷን ቆርጠው ህይወቷ ካለፈ በኋላ ሞተር ሳይክል እንዲመጣ ለ3ኛ አመልካች ደውለው ሬሳውን በሞተር ሳይክል ጫካ ውስጥ የጣሉ መሆኑንና አባሪ ተባባሪ በመሆን የግድያ ወንጀል የፈጸሙ መሆኑን በመጥቀስ የከሰሰ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክስ በ2ኛ፣ 3ኛ  4ኛና 5ኛ አመልካቾች ላይ የቀረበ ሲሆን በ1996 ዓ.ም በወጣውን የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና አንቀጽ 841/1//1 ን በመተላለፍ  ከላይ  በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት በፈጸሙት ሬሳ የማንገላታት ወንጀል ክስ ተከሰዋል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ………

Print
16463

Documents to download

  • 214184(.pdf, 1.04 MB) - 1133 download(s)