/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ማስተዋል ታዘበው እና ወ-ሮ አቻም ሙጬ የሰ-መ-ቁ 180761

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 86614 ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 0318665 የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 54250 ጥር 17 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረበቀቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት አባታችን በህይወት እያለ በ300 ብር ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶበት እየኖረበት የሞተ መሆኑ ምስክሮቻችን መስክረውልን እያለ የ2ኛ ተጠሪ ምስክሮች ከኛ ምስክሮች ባልተሻለ ሁኔታ የሰጡትን ምስክርነት ወስዶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡……..         

Previous Article እነ መቶ አለቃ ኩምሳ ጨመዳ፣ወ-ሮ ኡርጌ መርጋ እና አቶ ካሳሁን አድነው የሰ-መ-ቁ 188071
Next Article አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138
Print
14511