/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

እነ ሳባ አርአያ እና ወ-ሮ ወ-ሮ በሻዱ ያደቴ የሰ-መ-ቁ 182692

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች ነሐሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 299179 ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፣ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ዝናሽ ኪዳኔ በሰበታ ከተማ ቀበሌ 04 ጎጥ 6 ውስጥ የሚገኝ እና አዋሳኙ በክሱ የተገለጸ ስፋቱ 500 ካ.ሬ በሆነው መሬት ላይ የተሰራ ቁጥሩ 9251 የሆነ መኖሪያ ቤት የነበራቸው መሆኑን፤ የአመልካቾች እናት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ተጠሪዎቹ በቀን 25/03/2010 ዓ.ም ከአመልካቾች ፍላጎት ውጪ የቤቱን አጥር አፍርሰው በመግባት በቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች በጉልበት አስወጥተው ሁከት የፈጠሩባቸው መሆኑን በመግለጽ ይዞታውን  እንዲለቁ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡……..

Print
15850