/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

እነ ተማሪ የውብዳር ጫካ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰበር መ/ቁ/210256

ጉዳዩ የሥራ ላይ ጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ወላጅ አባታችን ሟች አቶ ጫካ ሰቦቃ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ የዶዘር ኦፕሬተር ሆነው በማገልገል በስራ ላይ እያሉ ህይወቱ በቀን 30/01/2001 ዓ.ም ያለፈ በመሆኑ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 110(3)(ለ) መሰረት የጉዳት ካሳና ለቀብር ማስፈፀሚያ የወጣ ወጪ ጨምሮ በድምሩ ብር 130,000.00 እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ በበኩሉ በሰጠው መልስ የአመልካቾች አባት የሞቱት በተጠሪ መ/ቤት ስራ ላይ እያለ ሳይሆን ሲሰሩበት የነበረው ዶዘር በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ካምፕ ውስጥ አቁመው ውቤ በሚባል ወንዝ ውስጥ ነው፤የአመልካቾች አባት የሞቱት በስራ ላይ እያሉ ነው ቢባል እንኳን የሟች ደመወዝ 2000 ብር ሳይሆን ብር 1273 መሆኑን ሊከፈላቸው የሚገባ ካሳ በአንቀጽ110(3)(ለ) መሰረት በ10% መጠን ለእያንዳንዳቸው ብር 7,650 ሲሆን ለቀብር ማስፈፀሚያ የሁለት ወር ደመወዝ ብቻ ነው በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ……            

Print
13192

Documents to download

  • 210256(.pdf, 849.09 KB) - 967 download(s)