Friday, July 22, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation እነ አቶ ሁሴን አሊ እንድሪስ እና ወ/ሮ ዘሀራ ዱሌቦ የሰበር መዝገብ ቁጥር 214803 ጉዳዩ ተጠሪ የሟቹ ሚስት መሆናቸውን እንዲሁም በሰበር ክርክሩ የሌሉት ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ የሟቹ ልጆች ስለሆኑ የሟች ሐጂ አሊ እንድሪስ ሙሳ ውርስ እንዲጣራ ውርስ አጣሪ እንዲሾምላቸው 1ኛ አመልካችን ተጠሪ በማድረግ አቤቱታ አቅርበው 1ኛ አመልካችም ውርሱ ቢጣራ እንዳማይቃወሙ መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ ቀሪዎቹ አመልካቾችም የሟቹ ልጆች መሆናቸውን በመግለጽ ጣልቃ ገብተው የውርስ ማጣራት ክርክሩ ተካፋይ ለመሆን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ውርሱ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ውርሱ ተጣርቶ ሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ አመልካቾች በሟቹ ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቁጥሩ 1588 የሆነው ቤት እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ቁጥሩ 1577 የሆነው ጋራዥ ቤት ተሸጦ የተገኘው ገንዘብ ሟች አባታቸው ሐጂ አሊ እንድሪስ ከሟቿ እናታቸው ወ/ሮ ዘውድነሽ ጋር በጋራ ያፈሩት ነው በማለት አስተያየታቸውን ስያቀርቡ ተጠሪ ሟች ንብረቱን ያፈሩት ከእሳቸው ጋር መሆኑንና ከሟቹ ጋር በጋብቻ ውስጥ እያሉ በቤት ቁጥር 1588 ላይ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ በማውጣታቸውንና ጋራዥ ቤት ተሸጦ በ1ኛ አመልካች እጅ የሚገኘው የሽያጭ ገንዘብ ግማሹ እንዲሰጣቸው ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ…….. Print 11695 Documents to download 214803(.pdf, 1.03 MB) - 913 download(s)