/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ አቶ ሰይፈ ላቀው እና አቶ አሸናፊ ተክሉ የሰ/መ/ቁ. 191393

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ከሳሾች፤ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩ የተጀመረው በቀይት ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካቾች በ09/07/2011 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የሟች እናታችንና አባታችን ወራሾች መሆናችንን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5 መሰረት ወራሽነታችንን አሳውጀናል፡፡ ነገር ግን ተጠሪ ሌላኛውን የስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ወ/ሮ ዘነበች ላቀውን ጨምሮ ያለ ህግ አግባብ የወላጆቻችንን መሬት ከጥር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ቦታው ስርጥ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን 4 ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ግመሎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን ½ ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ዳዲስ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን ¼፣ ሌሎች 2 ቦታ የሚገኙ 1/8 ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ዋደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውን 1/8 ጥማድ መሬትና ልዩ ቦታው አፋሳሽ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ¼ ጥማድ መሬት የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ ለቀው እንዲያስረክቡን እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Print
4097

Documents to download

  • 191393(.pdf, 962.32 KB) - 522 download(s)