/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141

እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141

ጉዳዩ የእቁብ ገንዘብ ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በጋምቤላ ክልል ማጀንግ ብሄረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን  ተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ በ1ኛ ተጠሪ ሰብሳቢነት እና በ2ኛ ተጠሪ ፀኃፊነት በየሳምንቱ የሚጣል እና የሚወጣ የጥምር የሚባል የእቁብ ማህበር በ2007 ዓ.ም መተዳደሪያ ደንብ እና መዝገብ ያለው የአንድ እጣ ብር 3000 ሲሆን እኔም በድርሻዬ የአንድ እጣና ግማሽ ማለትም ብር 4500 በየሳምንቱ እየጣልኩኝ በወቅቱ በደረሰብኝ ድንገተኛ የግድያ ሙከራ ወንጀል ጉዳት ደርሶብኝ መናገርና መንቀሳቀስ ሳልችል ለተከታታይ አራት ዓመት ቆይቼ ሊደርሰኝ የሚገባኝን ብር 166,500 ተጠሪዎች ከሰበሰቡ በኋላ ያልሰጡኝ በመሆኑ ከህጋዊ ወለድ ጋር በአንድነት እንዲከፍሉኝ እንዲወሰን የሚል ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸዉ አመልካች ሲከፍል የነበረው የአንድ ዕጣ መሆኑንና በደረሰበት አደጋ ምክንያት መናገር እና መፃፍ ባለመቻሉ የሚከፍለውን ሙሉ የአንድ ዕጣ በቀን 26/08/2007 ዓ.ም ያለ ዕጣ ዋስ በማስጠራት ዋስ አቶ ደረጀ ማዘንጊያ አማካይነት ብር 111,000 ተቀብሎ በዋሱ አማካይነት ሙሉ ዕቁቡን ገንዘብ በመክፈል ካጠናቀቀ በኋላ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ የዕቁቡ ማህበር አባል ሆኖ እያለ ያለአግባብ ለመበልፀግ ሲል ያቀረበው ክስ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ተከራክረዋል፡፡………..

Previous Article የእነ አምሳሉ አበራ እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361
Next Article እነ አቶ አየናዉ አላምረዉ ወ-ሮ መሰረት ሉሉ የሰ-መ-ቁ 183394
Print
15168