Tuesday, May 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation እነ አቶ ሽፈራው ሰለሞን(5) ወ/ሮ እየሩሳሌም ሐይላይ ሰዎች የሠ/መ/ቁጥር 252875 ጉዳዩ የስጦታ ውል ይፍረስልን ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በቀረበበት በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፤ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካቾች ያቀረቡት ክስም በአጭሩ፡- የአመልካቾች አያት የሆኑት ሟች ወ/ሮ ሐረጓ ተሰማ በሐረር ከተማ ሸንኮር ወረዳ ቀበሌ 10 የቤት ቁጥር 589 የሆነው ቤት ውስጥ ሲኖሩ ቆይተው በ2010 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው የውርስ ሀብት በሆነው መኖሪያ ቤት ላይ በ2003 ዓ.ም ያደረጉት ስጦታ ውል እንዲፈርስ በሚል ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ አመልካቾች ክስ ያቀረቡበት ቤት ቀደም ብሎ በሐረሪ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 48349 የውርስ ሀብት አይደለም ተብሎ ውሳኔ የተሰጠበት ስለሆነ በድጋሚ ክስ ሊቀርብበት አይችልም፤ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት የውርስ አካል አለመሆኑ ተረጋግጦ ክሱ ውድቅ በመሆኑ፤እንዲሁም ከተራ ቁጥር 2 እስከ 5 ያሉ አመልካቾች ወራሽ ስለመሆናቸው ሳያረጋግጡ ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት የሌለው መሆኑን፤ክስ የቀረበበትን ቤት በታህሳስ 11 ቀን 2003 ዓ.ም ሟች ለተጠሪ በስጦታ ካስተላለፉ ከ11 አመት በኋላ እንዲሁም አውራሽ የሖኑት ወ/ሮ ሐረጓ ተሰማ ከሞቱ አራት አመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ የታገደ ነው፤ ክሱ የቀረበለት የሐረሪ ክልል ህዝብ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም የሚሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ክርክራቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ… Print 1806 Documents to download 252875(.pdf, 863.38 KB) - 286 download(s)