/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

እነ አቶ ንጉሴ ወ/ማሪያም ወ/ሮ አሰለፈች ንጋቱ እና የሰ.መ.ቁ.213738

ጉዳዩ የቤት እና ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች ተከሳሾች፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቶች አስተዳደር ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 511 ቤት ግቢ በስተጀርባ ከደቡብ በኩል የተወረሰ እና 1ኛ ተጠሪ የምትኖበርበት የቤ.ቁ 510 የሆነ ቤት አለ፤ አመልካቾች እና 1ኛ ተጠሪ  በጋራ የምንጠቀምበትን መጸዳጃ ቤት 1ኛ ተጠሪ ያለአመልካቾች ፈቃድ በማፍረስ ሰርቪስ ቤት በመስራት እንዳንጠቀምበት አድርጋለች፤ 1ኛ ተጠሪ ማንም ሳይፈቅድላት ከምንኖርበት ቤት በስተሰሜን በኩል ከአመልካቾች ቤት ግድግዳ በማስጠጋት በግምት 100 ካ.ሜ አስፋፍታ ያጠረችውን አጥር እንድታፈርስ በተደጋጋሚ ተጠይቃ ፍቃደኛ አልሆነችም፤ 2ኛ ተጠሪም ከፕላን ውጪ ያለፈቃድ የተሰራውን እንዲያፈርስልን እንዲሁም የ1ኛ ተጠሪን ሕገወጥ ግንባታ አስቁሞ በሽንት ቤት የምናገኘውን አገልግሎት ወደ ነበረበት እንዲያስመልስን፣ 1ኛ ተጠሪ ወደ ይዞታችን ገብታ ያላግባብ ያጠረችውን አጥር እንድታፈርስ ጠይቀነው ለማስፈጸም ፍቃደኛ አይደለም፤ ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ  የተገነባውን ሰርቪስ ቤት እንድታፈርስ እና መጸዳጃ ቤቱን ወደ ነበረበት እንድትመልስ አስፋፍታ ያጠረችውን አጥር በተሰጠው የፕሮፖርሽን ካርታ መሰረት እንድታፈርስ፤ 2ኛ ተጠሪም የተሰራውን ግንባታ አስፈርሶ የጋራ መጸዳጃ  ቤት በ1ኛ ተጠሪ ወጪ ተሰርቶ አገልግሎት ላይ እንዲውል እንዲያደረግ አጥሩንም እንዲያስፈርስ ይወሰንልን ሲሉ  ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልም ንባብ ……..

Print
12786

Documents to download

  • 213738(.pdf, 850.67 KB) - 1649 download(s)