Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation እነ አቶ አመድ ሙሜ(2ሰዎች)የእና ወ/ሮ አሚናት ኡስማንሰ/መ/ቁጥር 254020 ጉዳዩ የገጠር መሬት ውርስን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት የሀረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ተከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ አውራሽ የሆኑት ወ/ሮ ከዲጃ ዑመር ከሳሽ ነበሩ፡፡ የአሁን ተጠሪ አውራሽ ያቀረቡት ክስም፡- ሟች አባታቸው በ1966 ዓ.ም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ሟች አባታቸው እርሳቸውንና ሟች ወንድማቸውን አቶ ዘከሪያ ኡመር የወለዱ መሆኑን፤ሟች ወንድማቸውም የአሁን አመልካቾችን እናት አግብቶ ሲኖር ቆይቶ ልጅ ሳይወልድ እና ሳይናዝ የሞተ መሆኑን፤ ለክርክር መነሻ የሆነው በአራት ቦታ የሚገኘው የገጠር መሬት የሟች አባታቸው እና ክፍፍል ያልተፈጸመበት እንዲሁም ከሟች ወንድማቸው ጋር ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆኑን፤ ሟች ወንድማቸው ከሞተ በኋላም የአሁን አመልካቾች እናት እየረዳቻቸው በመሬቱ ስትጠቀም እንደነበር፤ እርሷ ከሞተች በኋላ መሬቱን ተጠሪዎች እንዲለቁ ቢጠየቁ ፈቃደኛ ሊሆኑ አለመቻላቸውን ጠቅሰው መሬቱን ለቀው እንዲያስረክቡኝ እና ከመሬቱ የተገኘውን ጥቅም ጨምረው እንዲከፍሉኝ የሚል ነበር፡፡ ተጠሪዎች ለክሱ ባቀረቡት መልስ ክሱ በይርጋ የተቋረጠ ነው፡፡ ለክርክር መነሻ የሆነውን መሬት እናታችን መብት በመመስረት ንብረትነቱ የመንግስት በሆነ መሬት ላይ ከከሳሽ ወንድም ጋር ባልና ሚስት በመሆን ጋብቻው በሞት ቀሪ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ መብት ፈጥረው እየተጠቀሙ የቆዩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…. Print 2795 Documents to download 254020(.pdf, 832.14 KB) - 341 download(s)