Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation እነ አቶ አርአያ ዮሴፍ እና እነ ወ/ሮ አስናቀች መንግስቴ የሰ/መ/ቁ፡-210953 ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች በቀን 09/11/2013 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.376953 በቀን 8/11/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ሰሚው ችሎት እንዲታረምልን በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካቾች በአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ አሻሽለው ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በጋራ በመሆን በ2009 ዓ.ም ምንም መብት ሳይኖርቸው ከሚበቃ ከተማ ቀበሌ 01 ፍትሕ ጽ/ቤት አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኘውን 600 ካ.ሜ የሆነ 39 ቅጠል ቆርቆሮ በላዪ ላይ ያለውን ግምቱ ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ሊያወጣ የሚችል እና አወሳኙ በክስ ዝርዝር የተገለፀው በ1984 ዓ.ም እናቴ ወ/ሮ መንግስቴ ደስታ የምትባል የተናዘዘችልኝ ይዞታ በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.12873 በቀን 06/05/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዚህ ይዞታ ላይ ወራሽነትን አረጋግጬ ወንድሞቼ የሆኑትን ጣልቃ ገቦችን ውስጥ ትቼ በስራ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ከሄድኩ በኋላ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ በስራ ምክንያት ወደ አረብ ሀገር በመሄዷ ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ ይዘውብኝ ቤት ሰርተውበት እየነገዱበት ስለሆነ በራሳቸው ወጪ የሰሩትን ቤት አፍርሰው ይዞታውን እንዲለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡…….. Print 10911 Documents to download 210953(.pdf, 935.95 KB) - 893 download(s)