/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807

ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ  እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………

Previous Article አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326
Next Article እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406
Print
14598