Friday, February 25, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ ካሳሁን ዘላለም እና የሰሜን ሸዋ ዞን የገቢዎች ዓቃቤ ሕግ የሰ.መ.ቁ 208826 ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- 1ኛ አመልካች የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 06 ገቢዎች ጽ/ቤት በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት ተመዝግቦ በሬስቶራንት ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ በመስራት ላይ እንዳለ ሕዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 ሠዓት ሲሆን በሬስቶራንቱ ውስጥ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ለመጠቀም የገቡት አቶ ተክልዬ አስራት እና አቶ ብርቅነርህ ደሳለኝ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት ጥብስ፤ ሁለት ቢራ እና ሁለት ድራፍት ከተጠቀሙ በኋላ ለጥብሱ ብር 180፤ ለቢራው ብር 50፤ ለድራፍቱ ብር 24፤ በጠቅላላው ብር 254 / ሁለት መቶ ሀምሳ አራት / ከፍለው ሲወጡ ከሽያጭ መመዝገቢያው መሳሪያ የሚወጣውን ደረሰኝ ቆርጦ መስጠት ሲገባው ደረሰኙን ሳይሰጥ ግብይት የፈጸመ እና ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡………… Previous Article የቤጊ ከተማ አስተዳደር እና አቶ ደጉማ ባያ የሰ/መ/ቁጥር 205786 Next Article ወ/ሮ ፀሐይነሽ ወርቁ እነ አቶ አርአያ በዛብህ የሰ/መ/ቁ 211693 Print 10307 Documents to download 208826(.pdf, 1.05 MB) - 1788 download(s)