Tuesday, February 22, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪ ላይ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በተለያየ የቅጥር ዘመን በሽያጭ ባለሞያ የስራ መደብ ላይ ተቀጥረን ስንሰራ ብንቆይም ተጠሪ ከህግ ውጪ ከቀን 26/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ አሰናብቶናል፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ተጠሪው ካሳ፣ የአገልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ቅጣት፣ ከግንቦት ወር ጀምሮ የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስከሚበቃበት ጊዜ ድረስ ያለው የወር ደመወዛችን እና የዓመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡እንደሚከተልው ቀርቧል……………. Previous Article እነ አቶ ግርማ ገብራይ እና ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ የሰ/መ/ቁ፡-207081 Next Article እነ አቶ ከበደ ደሴ እና ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ የሰ/መ/ቁ.209757 Print 12727 Documents to download 209266(.pdf, 823.85 KB) - 1016 download(s)