Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation እነ አቶ ደለሳ ጅማ እና ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክስዮን ማህበር የሰ.መ.ቁ.214136 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ተከሳሾች የከሳሽ ማህበር አባላት ሁኖ የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎችን ባለመፈጸማቸዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ከማህበሩ እንዲሰናበቱ የወሰነ ሲሆን፣ ተከሳሾች ይህን ዉሳኔ ለማሰረዝ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነባቸዉ ሲሆን፣ በዚህ ዉሳኔ መሰረት ለማስፈጸም ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ክፍያ ያልከፈሉ አባላት ክፍያዉንና ቅጣቱን በሁለት ወራት ዉስጥ እንዲከፍሉ፣ ይህ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ በማስገባት ክፍያዉ ተሳስቦ እንዲከፈላቸዉ የተወሰነ በመሆኑ፣ ተከሳሾች ዉሳኔዉን ለማሰረዝ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነቸዉ ስለሆነ፣ ተከሳሾች አልከፈሏቸዉም ያለዉን ክፍያዎች በመዘርዘር፣ በጠቅላላ ጉባኤዉ ዉሳኔ መሰረት ከማህበሩ አባልነት እንዲወጡ ወይም እንዲሰረዙ እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ……. Print 10297 Documents to download 214136(.pdf, 254.62 KB) - 767 download(s)