Friday, November 8, 2024 / Categories: CASSATION, Cassation እነ አቶ ዳንኤል ተክለማርያም እና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሰበርመዝገብ ቁጥር 235267 ጉዳዩ የመንግስት የንግድ ቤትን ኪራይ የሚመለከት ሲሆን አቤቱታ ከ5ኛ አመልካች ዉጪ ሌሎቹ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የንግድ ቤት ኪራይ ዉል ስምምነት ያለን እና በንግድ ቤቱም ስንገለገል ቆይተናል አመልካቾች 2ኛ መመሪያ ከመዉጣቱ በፊት ሁለት የንግድ ቤቶችን መያዝ በሚፈቅደዉ ሕግ ወቅት የያዝነዉ ንግድ ቤት አዲስ መመሪያ በመዉጣቱ ምክንያት ይክለከላችዋል ማለቱ ሕግ ወደ ኃላ ሄዶ እንደማይሰራ የአለም አቀፍ ሰብሃዊ መብት ቃል ኪዳን፣ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት እና በወንጀል ሕጉ ተደንግጎ እያለ ይህን በመተላለፍ አመልካቾች በሕጋዊ መንገድ የያዝነዉን አንደኛዉን የንግድ ቤት መልሱ መባሉ ስህተት ስለሆነ ይታረምልን ያሉ ሲሆን 5ኛ አመልካች በበኩሉ እኔ የያዝኩት ንግድ ቤት ከ2ኛ አመልካች በሕጋዊ መንገድ ገዝቼ የተላለፈልኝን ተጠሪ 2ኛ አመልካችን ቤቱን እንድትመልስ መጠየቁ ሁከት አይደለም ተብሎ የተወሰነዉ እንዲታረምልኝ ብለዋል፡፡ መልካም ንባብ…. Print 317 Documents to download 235267(.pdf, 814.44 KB) - 66 download(s)