/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ አቶ ግርማ አዳነ እና ላልይበላ ንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 247702

የክሱ ይዘት በአጭሩ በላልይበላ ከተማ በንግድ ማህበር ተደራጅተን እየሰራን በሂደት 19 ክፍል የያዘ ሆቴል ገንብተን በለልይበላ ነጋዴዎች ማህበር ስም እየሰራን እያለ በአክሲዮን ሽያጭ ጠቅላላ ካፒታላችን ብር 2‚295‚500(ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሺ አምስት መቶ ብር) ስለደረሰ በ2002 ዓ.ም የማህበሩ ገንዘብ ያዥ የነበሩ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ  የ10 ሰዎችን አክሲዮን ገዝቻለው በሚል ከ10 ሰዎች ውጪ ባለነው በ21 አባላት ስም እንደ አዲስ ማህበር መመስረት አለብን በማለት ለማህበሩ ሀሳብ አቅርቦ ከሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የማህበሩ ስም ወደ ጌታቸው ግርማ እና ጓደኞቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚል ቀይሮ እየሰራ እያለ በማህበሩ አካላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮአል፡፡አመልካቾች እንደ ቁጥጥር ኮሚቴ አባልነታችን በመመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 8 በተሰጠን ስልጣን መሰረት የአመራር ግድፈቶች እንዲስተካከሉ የምናደርገውን ቁጥጥር በመቃወም የመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 4(2) ባላገናዘበ መልኩ አለአግባብ ከማህበሩ ስላሰናበተን ወደ ማህበራችን እንድንመለስ፣ወደ ማህበሩ የማንመለስ ከሆነም ንብረቱ ተጣርቶ በአዲስ መልክ ከተመሰረተበት ከ1997 ጀምሮ ማህበሩ ኦዲት ተደርጎ ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት የሚገኘው ድርሻችን እና ትርፋችን ታስቦ እንዲከፈለን የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ በአመልካቾች የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ፍ/ቤቱም ይርጋን በተመለከተ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በፍ/ህ/ቁጥር 448(2) መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ እንጂ ለማህበር ይፍረስልን እና ድርሻችን ይሰጠን ጥያቄ ላይ የሚቀርብ ስላልሆነ እንዲሁም ግንኙነታቸው በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የይርጋውን መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ መዝኖ የአመልካቾች ስንብት ህገ-ወጥ ስለሆነ ወደ ማህበሩ እንዲመለሱ እና ድርሻቸው ተካቶ የተሰራው የአክሲዮን ድልድል ታርሞ ክፍፍሉ ይፈፀም ሲል ወስኗል፡፡መልካም ንባብ….

Print
5223

Documents to download

  • 247702(.pdf, 853.18 KB) - 694 download(s)