Tuesday, February 22, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation እነ አቶ ግርማ ገብራይ እና ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ የሰ/መ/ቁ፡-207081 ጉዳዩ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ የውርስ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ የእናታችንን እና የአባታችንን የውርስ ይዞታ አዋሳኞቾቻቸዉ በክሱ ይዘት የተጠቀሱትን በአራት ቦታ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ ዉስጥ በ2000 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ መኖሪያ ቤት በጋራ እያስተዳደሩ ቆይተዉ ተጠሪ ድርሻችንን ሊያካፍሏቸዉ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ድርሻቸዉ አንዲያካፍሏቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ አመልካቾች የዉርስ ሀብት ነዉ የሚሉት መሬቶች ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ በግላቸዉ ይዘዉ የሚጠቀሙበት እንደሆነ መኖሪያ ቤቱንም በግላቸዉ የሰሩት እንደሆነ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡እንዲሁም የዉርስ ንብረት በአመልካቾች እጅ እንደሚገኝ በመግለጽ አመልካቾች እንዲያካፍሏቸዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡……. Previous Article ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እነ ገልገሎ ቀጀላ የሰ/መ/ቁ፡-206765 Next Article እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266 Print 9342 Documents to download 207081(.pdf, 1.04 MB) - 895 download(s)