/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ አቶ ግርማ ግያ እና አቶ አማረ ፍቅሩ የሰ-መ-ቁ. 186016

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር 1ኛ ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በአፈጻጸም ከሳሽ አቶ አበራ አላሮና በስር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች መካከል በሶዶ ከተማ መሀል ክፍለ ከተማ በ200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት እንዲሸጥ ሲታዘዝ የሥር 3ኛ ተከሳሽ የሆነው የሶዶ ከተማ መሀል ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሠጠውን መግለጫ በመቀየር ቤት የለውም ባዶ ቦታ ነው በማለቱ የአፈጻጸም ችሎቱ በንብረቱ ላይ የሠጠውን እግድ አንስቷል፡፡ በዚህ መካከል ንብረቱን ከአፈጻጸም ለማሸሽ በአመልካች ወኪልነት ቤቱን በብር 165,000.00 ሽጠውልኝ ቤቱን አፍርሼ ግንባታ የጀመርኩ ሲሆን ስመ-ሀብቱም ተዛውሮልኛል፡፡ አፈጻጸም ክርክሩ በይግባኝ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጥሎ ቦታው ላይ ቤት እያለው ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአፈጻጸም ውጭ መደረጉ ተገቢ አይደለም በማለት ቤቱ በሀራጅ ተሽጦ ለፍርድ ባለመብት አቶ አበራ አላሮ ዕዳ መክፈያ እንዲውል ወስኗል፡፡ ክፍለከተማው የተሰጠኝን ማስረጃ አመክኗል፡፡ ስለዚህ አመልካችን ጨምሮ የሥር ተከሳሾች ቤቱ በአፈጻጸም ክርክር ሂደት ላይ እንዳለ እያወቁ ከቅን ልቦና ውጭ አላግባብ ለመበልጸግ በማሰብና መብቴ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆኑ ለሽያጭ የከፈልኩትን ገንዘብ ብር 165,000.00 እና ለግንባታና ለሠነድ የወጣውን በድምሩ ብር 321,222.00 በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉኝ የሚል ነው፡፡ አመልካች ያቀረቡት መልስ ከሥር 2ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ዘውጋ በተሰጠኝ የውክልና ሥልጣን መሠረት ሕጋዊ ቤት በብር 65,000.00 ለተጠሪ ሽጫለሁ፡፡ የተሸጠው በብር 165,000.00 ነው የተባለው ሀሰት ነው፡፡ የተጭበረበረ ሽያጭ ሆነ አላግባብ የተገኘ ብልጽግና የለም፡፡ ጥፋት አልፈጸምኩም፤ ለክሱ ኃላፊነት የለብኝም ብለዋል፡፡ የሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የነበሩት ጉዳያቸው በሌሉበት ታይቷል፡፡……………

Previous Article እነ አቶ ፈልመታ አምቦ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ደምሴ የሰ-መ-ቁ 189090
Next Article ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
Print
15906

Documents to download