Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation እነ አቶ ጳውሎስ ኦርጂኖ እና አቶ ተስፋዬ ኤጌዶ የሰበር መ/ቁ/215762 ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዳይ ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በዱራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዲሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበሉ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውሉ መሰረት ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበሉትን ቀብድ አጠፌታ እና ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል መልካም ንባብ…….. Print 10144 Documents to download 215762(.pdf, 879.83 KB) - 881 download(s)