/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ አቶ ፈልመታ አምቦ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ደምሴ የሰ-መ-ቁ 189090

ጉዳዩ በቤት ሽያጭ ውል መሰረት ቤቱን አስለቅቆ ለመረከበ ዳኝነት ተጠይቆ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ በመሆን የአሁን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በአመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዛይድ መኮንን ላይ በመሰረቱት ክስ የስር 1ኛ ተከሳሽ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ በምስባክ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማኅበር ስም በካርታ ቁጥር 62/96/1119/90 ተመዝግቦ በተሰጠው ቦታ በማኅበር ተደራጅተው ተሸንሽኖ  በተሰጣቸዉ የቦታ ቁጥር 99 በሆነ 175 ካ/ሜ ቦታ ላይ የሰሩትን ጅምር ቤት በብር 145‚000.00 በቀን 29/12/1999 ዓ/ም በተደረገ ውል ሽጠውልኝ ቤቱን አስረክበውኛል፡፡ ተጠሪ በስር በ1ኛ ተከሳሽ እግር ተተክቼ ከቀን 03/13/1999 ዓ/ም ጀምሮ በአባልነት ለማህበሩ የሚከፈሉ መዋጮዎችን እየከፈልኩ ቆይቻለው፡፡የግንባታ እቃዎችን በማቅረብ የጅምር ቤቱን ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ እያለሁ የአሁን አመልካች ቤቱን ከስር 1ኛ ተከሳሽ ገዝቻለው በማለታቸው በፍ/ቤት ክርክር ተደርጎ በመ/ቁ 291299 ላይ በቀን 29/09/1999 ዓ/ም በተሰጠ ውሳኔ አመልካች ቤቱን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዘዋል ተብሎ ቢወሰንም አመልካች እስካሁን ድረስ ቤቱን በህገ-ወጥ መንገድ ይዘውብኝ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም አመልካች ያስከተሉብኝን የንብረት ባለቤትነት ክርክር የስር 1ኛ ተከሳሽ ተከራክረው በማስመለስ የውል ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲወሰንልኝ ፡፡ የአሁን አመልካች በሕገ-ወጥ መንገድ የያዙትን ቤት ለቀው እንዲያስረክቡኝ እንዲወሰንልኝ፡፡እንዲሁም አመልካች ቤቱን በሕገ-ወጥ መንገድ በመያዛቸው ያጣሁትን ገቢ አሰልቼ መጠየቅ እንድችል መብት ተጠብቆ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……….

Previous Article እነ አቶ አድማስ አደመ ከ የባህደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 189495
Next Article እነ አቶ ግርማ ግያ እና አቶ አማረ ፍቅሩ የሰ-መ-ቁ. 186016
Print
15143