/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ኡባህ በዲሪ ከ ኡመር ዩሱፍ ዶላል የሰ-መ-ቁጥር 190350

ጉዳዩ የጫት ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ የእዳ ይከፈለኝ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች እንደየቅደም ተከተላቸው ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ከአመልካቾች ጋር ባለን የጫት ንግድ ግንኙነት መነሻነት ጫቱን ቦንባስ አምጥቼ እያስረከብኳቸው ስንሰራ ቆይተናል፡፡ አመልካቾች ውሉን በራሳቸው ያቋረጡ ሲሆን ያለባቸውን የጫት ገንዘብ እዳ ብር 2,088,000 (ሁለት ሚሊዮን ሰማንያ ስምንት ሺ) እንዲከፍሉኝ ሽማግሌዎች ብልክባቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እና እዳው በሰነድ የተመላከተ ስለሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 284 መሰረት በተፋጠነ ስነ ስርዓት ገንዘቡን እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

Previous Article ወ-ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ-አ-ኤ-ካ ኃ-የተ-የግል ማሕበ የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ-ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ-ቤት የሰ-መ-ቁ. 161449
Next Article ወ-ሮ ተሚማ ሬድዋን በሽር እናአቶ በድሩ ሰማን፣አቶ ደሊል በድሩ የሰ-መ-ቁ 179231
Print
15329

Documents to download