Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation እነ እታለማሁ ተገኝ ኃ/ሚካኤል እና እነ ዮሴፍ ብርሃኑ ሞላ የሰ.መ.ቁ 210891 ጉዳዩ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የተሻሻለ ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በእነ እታለማሁ ተገኝ ሀ/ሚካኤል ተመዝግቦ የሚገኘውን የይዞታ መለያ ቁጥር AA000060502456 ካርታው የተሰጠበት ቀን 27/07/2011 ዓ.ም የቦታው ስፋት 368 ካ.ሜ የሆነ የንግድ ቤት ያላቸው መሆኑን፤ የንግድ ቤቱን በተመለከተ አመልካቾች ለወንድማቸው ለ1ኛ ተጠሪ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲከራይ እንዲያስተዳድር የውክልና ስልጣን የሰጡት መሆኑን፤1ኛ ተጠሪ የተሰጠውን የማስተዳደር ውክልና ስልጣን ያላግባብ በመገልገል በአነስተኛ ዋጋ ተከራይቶ አንዱን ክፍል በብር 30000 ከአስር ክፍሎች በላይ በድምሩ በብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ) በማከራየት ገቢውን በመሰብሰብ እየተጠቀመ እና የኪራይ ገንዘብ እንዳይቀበሉ የከለከላቸው መሆኑን በመግለጽ 1ኛ ተጠሪ የማስተዳደር ውክልና ከተሰጠው ጀምሮ የሰበሰበው የኪራይ ገቢ በአሁን ሰዓት በአካባቢ በሚከራዩ ቤቶች ሂሳብ ተሰልቶ እንዲከፍላቸው እና ቤቱን ለአመልካቾች እንዲያስረክቡ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ መልካም ንባብ………. Print 7993 Documents to download 210891(.pdf, 1.04 MB) - 659 download(s)