/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

እነ ወ/ሮ መሠለች ደስታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የሰ/መ/ቁ.193168

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ተከሳሽ እና ተጠሪ የመቃወም አመልካች ነበሩ፡፡አመልካቾች በዚህ ችሎት ደረጃ ተከራካሪ ባልሆነው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 582 በሆነ ይዞታ  ይ ያላቸው ካርታ እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ሲሉ የጠየቁት ዳኝነት በፍርድ ቤቱ ውደቅ በመደረጉ ይግባኝ አቅርበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ተመልክቶ አመልካቾች በዕጃቸው በሚገኘው 783.82 ካሬ ሜትር ይዞታ በመሆኑ ካርታውን እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ወስኗል፡፡………………..

Previous Article አቶ ደሣለኝ ሲሳይ እና ወ/ሮ ድማም ተክሉ የሰ/መ/ቁ፡-196963
Next Article አቶ ወንድማገኝ ታደሰ አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 198669
Print
12668

Documents to download

  • 193168(.pdf, 769.48 KB) - 893 download(s)