/ Categories: CASSATION, Cassation

እነ ወ/ሮ ሙሉእመቤት አምባቸው እና ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መ.ቁ.241751

ጉዳዩ ለህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ማጓጓዥያነት ውሏል ከተባለ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ መወረስ ጋር ተያይዞ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡የ1ኛ አመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/227926 ላይ ታህሳስ 04/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ፤ እንዲሁም የ2ኛ አመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/228134 ላይ ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበውም ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጭነው ተገኝተዋል በተባሉት የአሁን አመልካቾች ተሽከርካሪዎች ላይ የውርስ ትዕዛዝ ለመስጠት አመልካቾች ስለተጫነው እቃ ምንነት የነበራቸውን እውቅና ማረጋገጥ አስፈላጊ አይደለም በሚል ምክንያት ተሽከርካሪዎቹ ተወርሰው ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ከጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይምለግንዛ ቤ እንጂ ለፍርድ አ ፈጻ ጸምዓላማአያገ ለግልም! ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 21 እና 22 እንዲሁም ከጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 147 አንፃር መርምሮ ለመወሰን ነው፡፡ጥሩ ንባብ.... 

Print
345

Documents to download

  • .241751(.pdf, 1.07 MB) - 62 download(s)